ሀገሬ ቲቪ

ሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ስራ ተመለሰ

በሶማሊያ ተዘግቶ የነበረው የሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ስራ ተመለሰ።

36 ተሳፋሪዎችና ሠራተኞች ጭኖ ሲጓዝ የንበር አውሮፐላን አደጋ ከደረስበት በኋላ አወሮፐላን ማረፊያው ለበረራ ዝግ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ከአደጋው ሁሉም ሠራተኞችና መትረፋቸውን ያሳወቀው የሶማሊያ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን፤ መንሳኤው እየተጣራ ነው ብሏል፡፡

ባለስልጣኑ እንዳስታወቀው የአውሮፕላን ማረፊያው አደጋው ከደረሰ ከሁለት ሰዓት በኋላ ተመልሶ ተከፍቷል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሶማሊያ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ለአደጋው ለሰጡት ፈጣን ምላሽ ምስጋናውን ቸሯል ሲል ዋሽንግተን ፖስት ጽፏል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-07-19