ሀገሬ ቲቪ

የ 8 ዓመት ልጅ የአካል መጠን ያላት የ 22 ዓመቷ እንስት

ፊቷን ሲያዩ ገና ሮጣ ያልጠገበች በመቦረቂያ እድሜዋ ላይ የምትገኝ ዕድሜዋ ስንት ነው ብንሎት ምን አልባት 7 ካበዙትም 10 የሚሉላት ናት።

ነገሩ ግን በተቃራኒው ነው ሻውና ትባላለች የ22 ዓመት ወጣት ስትሆን የ አካልዋ መጠን ግን የ8 ዓመት ልጅ ነው።

የሻውናን ህክምና ሲከታተሉ የነበሩ ባለሞያዎች የዚህ ችግር መንስኤ ምንድነው ሲባሉ ይህ ነው ለማለት ባያስደፍርም በልጅነቷ የተከሰተባትን የአንጎል ካንሰር ህመም ለማዳን የተደረገላት ሕክምና ምናልባትም ዕድገትዋን ገድቦት ሊሆን ይችላል ይላሉ ።

ሻውና ይህ የካል መጠኗ የልጅ መምሰሉ ከፍተኛ የስነ ሎቦና ጫና እንዳሳደረባት ትናገራለች ።

በ አንድ ወቅት ለመገናኛ ብዙሃን ሀሳቧን ስትገልጽም “እኔን ሲመለከቱኝ ፣ ገና የ አንደኛ ክፍል ትምህርቷን የምትከታተል፤ በቤተሰብ ቁጥጥር ስር የሆነች እና ምንም ሀሳብ የሌለባት ህጻን ልጅ እመስላቸዋለሁ ።” “እውነታው ግን ይህ አይደለም እኔ ትንሽ ልጅ አይደለሁም በ22 ዓመቴ የ8 ዐመት ልጅ አካል የያዝኩ ሴት ነኝ ። ምንም እንኳ በአካል ማደግ ባልችልም እንደ ትልቅ ሰው መታየት ና በ ዕድሜዬ ክብር ማግኘት እፈልጋለሁ” ብላለች ።

እንደማንኛውም ሰው በ በመዝናኛ ቦታዎች ጊዜዋን ለማሳለፍ ፤ የፍቅር ጓደኛ ለመያዝ እንዲሁም ስራ ተቀጥሮ ለመስራት ዕድሜዋ ቢፈቅድላትም እነዚህን ማድረግ ግን በጣም ከባድ እንደሆነባት የምትናገረው ሻውላ እባካቹሁ ነጻነቴን ስጡኝ ስትል የ አካባቢዋን ነዋሪዎች ተማጽናለች ።

ይህ የሻውና ታሪክ ምን አልባትም በአለም ላይ ሲከሰት የመጀመሪያው አይደለም ከጥቂት ዓመታት በፊት ዙ ሼንካይ የተባለ የ 34 ዐመት ግለሰብ የ አካል መጠኑ የ 14 ዐመት ልጅ መምሰሉ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃኖች ተዘግቧል። ይህም ሰው የሰውነት እድገቱ ሊቆም የቻለው ልክ እንደ ሻውና በልጅነቱ በጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት እንደሆነ የህክምና ባለሞያዎች ተናግረዋል ።

እንደዚህ አይነት ችግር በተለያዩ የ አለማችን ክፍሎች የሚስተዋሉ ሲሆን በኛው ሀገርም እድሜያቸውን ቀድመው ከሚገባቸው በላይ የአካል መጠን የያዙ እንዲሁም እድሜያቸው ቀድሞአቸው የ ልጅ ገጽታን የተላበሱ ሰዎች መኖራቸው ይስተዋላል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-07-19