ሀገሬ ቲቪ

ይፋ የሆነው የታሪፍ ማሻሻያ

በሚኒባሶች እና ታክሲዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሆነ:: የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የታሪፍ ማሻሻያን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በማሻሻያውም በሚኒባስ (ቅጥቅጥ ወይም ሃይገር ባስ) የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ በሚኒባስ በኪሎሜትር ከ40 ሳንቲም ወደ 45 ሳንቲም ከፍ የተደረገ ሲሆን፤በታክሲ ደግሞ በኪሎሜትር ከ90 ሳንቲም ወደ 1ብር ከፍ ብሏል፡፡ በሚኒባሶች የተደረገው ጭማሪ ዝቅተኛው 1 ብር ሲሆን፤ ከፍተኛው ደግሞ 2 ብር ሆኗል፡፡ በታክሲ ላይ የተደረገው ጭማሪ ዝቅተኛ 50 ሳንቲም ሲሆን ፤ከፍተኛው ጭማሪ 3 ብር ከ50 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡ ጭማሪው የኪሎሜትር ርቀትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ በመግለጫው ተገልጿል፡፡ የታሪፍ ጭማሪው በብዙሃን ትራንስፖርት ላይ እንዳልተደረገ የከተማው የትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ በመግለጫው አሳውቋል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-17