አዲስ አበባን ከትንባሆ ጭስ ለማድረግ፤ ዜጎቿም ጤናማ እንዲኾኑ የሚረዳ ንቅናቄን ከጀመረች ሰንበትበት ብላለች። የአዲስ አበባ ምግብ እና መድኀኒት ባለሥልጣን ደግሞ ይህን ንቅናቄ ይመራል።
የዚህ ንቅናቄ መጀመር የተወሰኑ ለውጦችን ማስገኘቱን የአ.አ ምግብ እና መድኀኒት ባለሥልጣን ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት በዳዳ ለጣቢያችን ተነግረዋል። ይሁን እንጂ ከተቋማት መናበብ ጀምሮ የተለያዩ ክፍተቶች መኖራቸውን ገልጸዋል።
የአንድ ዓመት ተኩል እድሜን የያዘው ንቅናቄ በሙከራ ደረጃ በአራዳ እና ቦሌ ክፍለከተሞች ከተጀመረ በኋላ በሌሎችም ክ/ከተሞች ተግባራዊ እንዲኾን ተደርጓል።
በከተማው ትንባኾ አምራች ፋብሪካ እያለ ንቅናቄውን ተግባራዊ ማድረጉ ውጤታማ ይኾናል ወይ ስንል ወ/ሮ ትዕግስትን ለጠየቅናቸው ጥያቄ
“በዋናነት እንቅስቅሳኤው የትንባሆ ተጠቃሚውን ቁጥር መቀነስ ነው ትንባሆ እንዳይመረት አናደርግም” ብለውናል።
አዲስ አበባን ከትንባሆ ጭስ ነጻ የማድረግ ንቅናቄን ከሚደግፉት ተቋማት መካከል መቋሚያ የማኀበረሰብ ልማት ድርጅት አንዱ ነው። በተቋሙ የፕሮጀክት ማኔጀር አቶ ኢሺሳ መንግሥቱ ተቋማቸው አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ እያገዘ ነው ብለዋል።
ንቅናቄው ከተማዋ ከትንባሆ ጭስ በሚገባ ነጻ እስከምትሆን ይቀጥላል ተብሏል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-07-19
