በዓለም አቀፍ ደረጃ የቼዝ ቀን ሐምሌ 20 ይከበራል። የቼዝ ጨዋታ ወይም ስፖርት የተጀመረበት ሀገር ይህ ነው ተብሎ ለመናገር አሻሚ እንደኾነ ነው የሚነገረው።
በርካታ ጥናቶች ግን የቼዝ ስፖርት በእስያ አህጉር በህንድ፣ ቻይና፣ ሩሲያ እና ማዕከላዊ እሲያ ውስጥ አካባቢ እንደተጀመረ ያመላክታሉ።
የቼዝ ስፖርት በኢትዮጵያም ከ500 ዓመት ዓመት በፊት እንደተጀመረ ይነገራል። በንጉሳዊ አስተዳደር የነበሩ መሳፍንቶች እና አለቃዎች በቤተመንግሥት ሠንጠረዥ በሚል ስያሜ ይጫወቱት እንደነበር የኢትዮጵያ ቼዝ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰይፉ በላይነህ ነግረውናል።
አኹን ላይ ስፖርቱ የእድሜውን ያህል ሰውጋር ደርሷል ባይባልም የተሻለ ለውጦች ስለመኖራቸው አቶ ሰይፉ ገልጸውልናል።
ወደ 200 የሚጠጉ እና እውቅና የተሰጣቸው የቼዝ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያ እንደተሳተፈች ሰምተናል። እነዚህ ውድድሮች ላይ የሚሳተፉ ክለቦች በይፋ መመስረት የጀመሩትም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነበር።
በቅርቡ ወደ በህንድ ቼናይ 44ው የቼዝ ኦሎምፒያድ ኢትዮጵያን ወክለው ለመሄድ ልምምድ ላይ ናቸው። ስለዝግጅታቸው ጠይቀናቸው እስካሁን ስልጠና ባይሰጠንም በራሳችን ልምምድ እያደረኝ ነው ብለውናል።
እነዚህ በዓለም አቀፍ የቼዝ ውድድሮች ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ስፖርቱ እንዲጎለብት ራሱን የቻለ የመጫዎቻ ቦታ አንስቶ በርካታ መሟላት ያሉባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ነግረውናል።
ከቀናት በኋላ በህንድ ቼናይ በሚካሔደው 44ው የቼዝ ኦሎምፒያድ ውድድር ኢትይጵያን ወክለው ሊሚሄዱት ለነዚህ ተጫዎቻችን ጣቢያችን ሀገሬ ቴሌቭሽን ጥሩ እድል እንዲገጥማቸው ከወዲሁ ይመኛል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-07-20
