ሀገሬ ቲቪ

“ሩስያ የዩክሬይን ግዛቶችን የመጠቅለል ዕቅድ አላት” አሜሪካ

በዩክሬን ጉዳይ ፣አሜሪካ ከሩስያ ጋር የጀመረችው ውዝግብ ተካሮ ቀጥሏል። ሩስያ ዩክሬንን ልትወር ትችላለች የሚል ስጋት አለኝ የምትለው አሜሪካ በሩስያ ላይ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅቻለሁ ስትል ቆይታለች።

አሁን ደግሞ አሜሪካ ሩሲያ ተጨማሪ የዩክሬንን ግዛት ለመጠቅለል እንዳቀደች እና ዩክሬናውያን ለሩሲያ ዜግነት እንዲጠይቁ እያስገደደች ነው ስትል ወቀሳለች።

የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢይ እንደተናገሩት ሩሲያ የዩክሬንን ተጨማሪ ግዛት ለመጠቅለል እየሰራች ነው ብለዋል።

ሩሲያ ክሪሚያን የያዘችበትን አካሄድ በመድገም ተጨማሪ የዩክሬንን ግዛት የራሷ ለማድረግ ውጥን ይዛለች። ቃል አቀባዩ ኪርቢ ለጋዜጠኞች ይህንን ተናግረዋል

“ሩሲያ ተቆጣጥራ የያዘቻቸውን አካባቢዎች ለመጠቅለል እስከ ጎጎሮሳውያኑ መስከረም ድረስ የሕዝበ ውሳኔ አደረኩ ለማለት ያህል ልታደርግ ትችላለች ብለዋል።ሩሲያ በስፋት ሕገ-ወጥ ተብሎ የሚተች የታይታ ሕዝበ ውሳኔ አድርጋ ክሪሚያን ከዩክሬን የወሰደችው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ 2014 ነበር። ጉዳዩን ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን። ማንም ሰው በዚህ አይሽወድም ሩሲያ ያረጀና ያፍጀ ስልት እየተከተለች ነው።” br>
ቃል አቀባዩ ሩሲያ ከዩክሬን የጠቀለለቻቸውን ክልሎች ለማስተዳደር ባለሥልጣናትን ሾማለች ሲሉም ተደምጠዋል።ይህ እርምጃም ግዛቶቹን የግሏ የማድረጓ እንቅሥቃሴ አንደኘው ተቀጥያ ነው ብለዋል።

የሕዝበ ውሳኔውን ድምጽ ውጤትም ሩሲያ የዩክሬንን ሉዓላዊ ግዛት ለመጠቅለል ትጠቀምበታለች ብለዋል ቃል አቀባዩ።ሩሲያ በራሷ አካል ባደረገቻቸው የዩክሬን ግዛቶች የሩሲያ ባለስልጣናትን መሰየሟን ቢዝነስ ኢንሳይደር ጽፏል ።

ሩሲያ ክሪሚያን በሕዝበ ውሳኔ የራሷ አካል ማድረጓ ሕገ-ወጥ ተደርጎ በበርካቶች መታየቱን ዴሊ ሜል ዘግቧል።በዚህ ድምጸ ውሳኔ በርካታ የዩክሬን ደጋፊዎች ድምጽ ላለመስጠት አድማ መትተው የነበረ ሲሆን ሕዝበ ውሳኔው ነጻ እና ፍትሐዊ አልነበረም።

በቀጣይ በሌሎች የዩክሬን ግዘቶች የሚካሄዱ ሕዝበ ውሳኔዎችም ተመሳሳይ ነው የሚሆኑት። ሩሲያን ለመቀላቀል የሚቃወሙ ተቃዋሚዎች ድምጻቸው ይታፈናል ሲሉ የአሜሪካ ባለስልጣናት ትችታቸውን እያቀረቡ ነው ።

የሩሲያን እቅድ እያጋለጥን ነው የሚሉት ቃላ አቀባዩ ግዛት የመጠቅለሉ እቅድ ሕገ ወጥ እና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ዓለም ታቅውቃለች ብለዋል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-07-20