ሀገሬ ቲቪ

650 የህንድ ኩባንያዎች በኢትየጵያ ኢንቨስት እያደረጉ ነው

በኢትዮጵያ የህንድ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት መጠን 5 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተመላከተ። ይህ የተባለው በኒው ደልሂ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የህንድ -አፍሪካ የንግድ ትብብር ጉባኤ ላይ ነው።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የውጭ ሀገራት ኢንቨስትመንት ህንድ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ኩባንያዎቹ በአጠቃላይ ከ75 ሺሕ በላይ ለሆኑ ሰዎች የስራ እድል በመፍጠር ከውጭ ኩባንያዎች በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የህንድ-አፍሪካ ትብብር ስብሰባ በየዓመቱ ይካሄዳል።

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-20