በጋምቤላ ከተማ በፀጥታ መደፍረስ ተጥሎ የቆየው የሰዓት እላፊ ገደብን ማንሳቱን የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በከተማው የሰዎች እና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴን በመለየት ጽ/ቤቱ ከአንቡላንስና ከፀጥታ ሀይል ተሽከርካሪ በስተቀር ማንኛውም ተሽከርካሪና ሰዎች መንቀሳቀስ የሚችሉት ከንጋቱ 11፡30 እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት መሆኑን ገልጾ ነበር።
ሰሞኑን በጋምቤላ ከተማ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ከቀናት በፊት ተጥሎ የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ መነሳቱን አስታውቋል።
በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-20
