ሀገሬ ቲቪ

ሩሲያ እና ኢራን የ40 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት አደረጉ

የሩሲያዉ ነዳጅ አምራች እና የኢራን ነዳጅ ኩባንያ 40 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ከዚህ ውስጥ 20 ሚሊዮኑ ለኪሽ እና ለሰሜናዊ ፓርስ የጋዝ ማምረቻ የሚከፋፈል ሲሆን፣ በቀን የ100 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ተጨማሪ ጋዝ እንዲያመርቱም ይረዳል ተብሏል።

ኢራን ከሩሲያ በመቀጠል በዓለም ሁለተኛዋ ከፍተኛ የጋዝ ክምችት ያላት ሀገር ብትሆንም፣ የአሜሪካ ማዕቀብ ከቴክኖሎጂ ጋር ግንኙነት እንዳይኖራት ያቀባት በመሆኑ ወደ ዉጭ የሚላከዉ የጋዝ ዕድገት አዝጋሚ ነው።

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-20