ሀገሬ ቲቪ

ኔትፍሊክስ ደንበኞቹን እያጣ ነው

ኔትፍሊክስ ከሚያዚያ እስከ ሀምሌ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ አገልግሎቱን የሚያቋርጡ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ መሄዱን ጠቁሟል።

በዚህ ሳቢያም የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ሾዎችን፣ ፊልሞችን እና ዶክመንታሪዎችን የሚያቀርበው ኔትፍሊክስ አንድ ሚሊዮን ደንበኞቹን አጥቷል።

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በ25 ዓመት ታሪኩ ያጋጠመው ኪሳራ በእጅጉ ትልቁ ነው ተብሏል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞቹን ለመቀነስም ተገዷል።

ኔትፍሊክስ ደንበኞቹን ቢያጣም 1.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያገኘ ሲሆን ገቢው ካለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ጋር በንጽጽር 9 በመቶ እድገት በማሳየት ወደ 8 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ከፍ ብሏል።

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-20