በዓልን ምን በወጣዎት ምግብ በማብሰል ተጠምደው በስራ ያሳልፋሉ ለዚህ መላ አለን እያሉን ነው። ምግብን የሚያበስሉ ሮቦቶች አሉላችሁ ብሎናል አንድ የሮቦት አምራች ኩባንያ። እነዚህ ሮቦቶች በጣርያው ግድግዳ ላይ በሚገጠም ሀዲድ መሰል መጓጓዣ በመጠቀም በማዕድ ቤት ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ያሰኞትን አብስለው ያቀርቡሎታል። መቀመጫውን ለንደን ያደረገ ሞሊ ሮቦቲክስ የተባለ ኩባንያ ነው ሮቦቶቹን ያመረታቸው። አነዚህን ሮቦት ሼፎች በሚቀጥለው ዓመት ለገበያ አቀርባቸዋለው ብሏል። ኩባንያው እነዚህን የማዕድ ቤት ባለሙያዎች ለማጎልበት የ2011 የቢቢሲ ማስተር ሼፍ አሸናፊ የሆነውን ቲም አንደርሰንን ቀጥሮለታል። ታዲያ ሮቦቱ የሰውየውን የማብሰል ጥበብ እየኮረጀ እራሱ ደግሞ እንዲሰራ የሚያስችል ፕሮግራም ተጭኖበታል። ኩባንያው በዚህ መንገድ ወጥነት ያለው ማብሰል የሚችል ሞያተኛ ሼፍ ሮቦት አዘጋጅተናል ማለቱን ሲል ቢቢሲ አስነብቧል። ሮቦቱ በፊት መስታወት ላይ በተገጠመ ስክሪን የሚፈልጉትን መርጠው ያዙታል። ሮቦቱም በማዕድ ቤት ውስጥ ተንቀሳቅሶ መጥበሻ አግሎ፣ ሽንኩርት ከትፎ፣ ድንች ልጦ ክሽን አድርጎ አብስሎ ይመግቦታል። ባለ ሁለት እጅ ሮቦቱ ከ 5 ሺሕ በላይ የምግብ አይነቶችን ጣት እንዲያስቆረጥም አድርጎ ማብሰል ይችላልም ነው የተባለው።
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-20
