ሀገሬ ቲቪ

ሀያ ስድስት መጋዘኖች ታሸጉ

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ካሳሁን ጎፌ ወደ ውጭ የምንልካቸው ምርቶች በአብዛኛው ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚውሉትን አይደለም ያሉ ሲሆን የሀገር ውስጥ ፍጆታ ላይ የምርት ማከማቸት ችግር ስለመፍጠሩ ገልጸዋል።

“ኤክስፖርት የምናደርጋቸው የግብርና ምርቶች አብዛኞቹ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚውሉ አይደሉም። ዋና ፈተና የሆነብን ምርትን አከማችቶ በመጋዘን መያዝ ነው።”

ሚኒስትር ዲኤታው አክለውም ምርት በሚያከማቹ ላኪ ድርጂቶች ላይ እርምጃ እንደተወሰደም ተናግረዋል።

“እስካሁን ምርት ያከማቹ 26 የላኪ ድርጂቶች መጋዘኖች ታሽገዋል።”

ሚኒስትር ዲኤታው አቶ ካሳሁን ከላኪ ድርጂቶች በውጭ ንግድ ከስሮ የመሸጥ የተሳሳተ እሳቤ እንዳለም ጠቁመዋል።

“በወጭ ንግድ አክስሮ በገቢ ንግድ ከዶላር አተርፋለሁ የሚል የተሳሳተ እሳቤ አለ። ንግድ ነው፤ኤክስፖርት የሚያደርግ ከኤክስፖርት ለማትረፍ መነገድ ይኖርበታል።”

ይሄው የተሳሳተ እሳቤ ከውጭ የሚገቡ ንግዶች ዋጋቸው ያለአግባብ እንዲንር በማድረግ የሀገር ኢኮኖሚን ይጎዳል ብለዋል።

አቶ ካሳሁን መስሪያ ቤቱ የዓለም ገበያ ሁኔታን አጥንቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መክሮ የመላኪያ ዋጋን እንደሚያወጣ የጠቆሙት ሚኒስቴሩ ከላኪ ድርጅቶች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ካወጣው ዋጋ በታች የመሸጥ ፍላጎት ያላቸው እንዳሉ ተናግረዋል።

ስለ ጉዳዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከላኪ እና አስመጭ ድርጂቶች ጋር መክሮ መግባባት ላይ እንደደረሰም ሚኒስተሩ ጠቁመዋል። ከወጭ ንግድም በ2014 በጀት ዓመት ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።

ስለ ጉዳዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከላኪ እና አስመጭ ድርጂቶች ጋር መክሮ መግባባት ላይ እንደደረሰም ሚኒስተሩ ጠቁመዋል። ከወጭ ንግድም በ2014 በጀት ዓመት ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።

በአብርሃም በለጠ
2022-07-21