ሀገሬ ቲቪ

በሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት በርካታ ዜጎች ተገድሉ

ጎረቤት ሀገር ሱዳን በተለያዩ በውስጥ የፖለቲካ ጉዳዮቿ እስካሁን እየታመሰች ትገኛለች። የጀነራል ቡርሀን መንግሥት የሲቪል መንግሥቱን በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ማስወገዳቸውን ተከትሎ የተከሰተው የሕዝብ አመጽ ሳይበርድ የእርስ በእርስ ግጭት ሌላው ፈተና ኾኗል።

ከቀናት በፊት በሱዳን የመሬት ይገባኛልን መሠረት ባደረገው እና ወደ ጎሳግጭት በተለወጠው ክስተት የሟቾች ቁጥር አንድመቶ አምስት መድረሱ ተሰምቷል።

በብሉ ናይል ግዛት ከሳምንት በፊት በተነሳው በዚህ ግጭት ከ290 በላይ ሰዎ ደግሞ መጎዳታቸውን የሱዳን ጤናሚኒስቴር ተነግሯል። በበርቲና ሀውሳ በተባሉ ጎሳዎች መካከል የተፈጠረ ግጭት ነው ለንጹሀኑ ሞት መክንያት የኾነው።

ኹለቱ ጎሳዎች ለበርካታ ጊዜአት በመሬት ይገባኛል አሊያም በወሰን ምክንያት ጦር ሲማዘዙ ቆይተዋል። የአሁኑ ግጭት ዋና መነሾ ችግራቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሀውሳ ጎሳ ያቀረበውን የመፍትሔ ዐሳብ የበርቲ ጎሳ አልቀበልም ማለቱን ተከትሎ ነው ተብሏል።

የሀውሳ ጎሳ የመሬት ንብረትነትን የሚቆጣጠር ሲቪል ባለሥልጣን እናቋቁም የሚል ሀሳብን ነበር ያቀረበው። ነገር ግን ይህ መፍትሔ ጎሳው መሬታችንን ለመንጠቅ የሚደረግ ነው ሲሉ እንዳልተቀበሉት የበርቲ ጎሳ አባል የኾነ አንድ ባለሥልጣን መነጋሩን ሲጂቲኤን ዘግቧል።

አኹን ላይ በብሉናይል ግዛት ግጭቱ እንደቆመና አንፃራዊ መረጋጋት እንደተመለሰ ቢነገርም በሌሎች ግዛቶች ግን ውጥረት ተባብሷል። የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ጀማል ናስር ኤፍፒሲ ለተሰኘው የዜና ምንጭ በስልክ በሰጡት መረጃ ኹሉም ነገር ወደ ቀዶሞ ሰላሙ ተመልሷል፤ አሁን ላይ ያለው ፈተና ተፈናቃዮችን ወደ ቀድሞ ቦታቸው መመልስ እና መጠለያ ማዘጋጀቱ ላይ ነው ብለዋል። የተባበሩት መንግሥታት በዚህ ግጭት ከ17 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል። 14 ሺ የሚኾኑት በሦስት ትምህርት ቤቶች ተጠልለዋል።

የተጎዱ ሰዎችን ለመታደግ ሆስቲታሎች የደም ለግሱን ጥሪ እያደሩ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና መስጫ መሣሪያዎች በማለቃቸው የጤና ተቋማት አስፈላጊውን ዕርዳታ መስጠት ተቸግረናል ብለዋል። ከጊዜ ወደ ጊዜ የተጎዱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መኾኑንም ተናግረዋል።

በሱዳን ድንበርን ምክንያት የሚያደርገው ግጭት ከውስጥ ጉዳይ አልፎ ከጎረቤት ሀገር ጋር ጠብ የሚያስጭራት ጉዳይ ነው እንደአብነትም ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ውጥረት ማንሳት ይቻላል።

ከ1894 ዓ.ም. የሚጀምረው የአል-ፋሻጋ ግዛት ይገባኛል ውዝግብ አንዴሞቅ አንዴ ድሞ በረድ እያለ እስከዛሬ ቆይቷል።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ጦርነት ሱዳን አጋጣሚውን በመጠቀም ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ሰተት ብላ መግባቷ ይነገራል። የሱዳን ገዢ ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ ሌተናንት ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን በትግራይ ጦርነት ሲጀመር ከፍተኛ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ማሰማራታቸው ተዘግቧል።

ሱዳን በኢትዮጵያ ተይዞብኛል የምትለውን መሬት በኃይል ማስመለሷን መነገሯ ይታወሳል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-07-21