ሀገሬ ቲቪ

ተላላፊ ያልሆኑ ሕመሞች ህክምና በመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ሊጀመር ነው

በተደጋጋሚ እንደሚገለጸው በኢትዮጰያ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች በእጅጉን እየጨመሩ ነው። እንደ ካንሰር ፣የልብ ህመም፣ ስኳርና የመተንፍሻ አካላት ላይ የሚፈጠሩ ሕመሞች ዋነኞቹ ናቸው።

የዓለም ጤና ድርጅት ገዳይነቱ አሳሳቢ ነው በሚል “ደብሊው ኢች ኦ ፔን” የተሰኘ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ በፕሮጀክቱ እንደ ደም ግፊት፣ ስኳር፣ የመተንፍሻ አካላት ህመም እና የመሳሰሉትን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ተቋማት ላይ በጤና ጣቢያዎች ላይ እንዲስጥ አስጀምሯል።

በማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ በጤና ሚኒስትር፣ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል ጤና ቢሮና ኤንሲዲ ፖቨሪቲ ኔት ወርክ በተገኘ የገንዝብ ድጋፍ ከዚህ በተሻለ በመጀመሪያ ደረጃ ሆሰፒታሎቸ ላይ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ለታካሚዎች ምላሽ የሚስጥና እና የታካሚዎችን እንግልት መቀንሰ የሚያስችል ፔን ፕላስ የተሰኘን ፐሮጀክት ተግባራዊ እንድሚደረግ የማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዱ በቀለ ለሀገሬ ገልጸዋል።

ለሁለት ዓመታት በሙከራነት በሚቆየው በዚህ ፕሮጀክት 35 ሚሊዮን ብር ፈሰስ የሚደርግበት ሲሆን፣ በተመረጡ በኦሮሚያ የሙከጡሪ ሆሰፒታል፣ በአማራ ደግሞ የአዲስ ዘመን ሆሰፒታል ሥራ ለመጀመር ትልልቅ የመመርመሪያ ማሽኖች እንደሚገጠምላቸው፣ መድሃኒቶችም ተደራሽ እንደሚደረግ በጤና ሚንስቴር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ቡድን ከፍተኛ ኅላፊ ዶ/ር ሙሴ ገ/ሚካኤል ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ባለሞያዎችን በማሰልጠን፣ ጠቃሚ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ በ2 ሆሰፒታሎች የሚጀመረውን “ፔን ፕላስ” የተሰኘውን ፕሮጀክት መንግሥትም ጉዳዩን በትኩረት ተመልክቶ ወደ ሌሎች ሆሰፒታሎች በማዳርስ መፍትሄ ለመሆን መሰራት እንዳለበት የካንሰር ሶሳይቲው ዋና ዳይሬክተር ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፔን ፕላስ ትግበራ ማሳያ ፕሮጀክት በብሔራዊ ደረጃ በይፋ የማሰጀመሪያ ስነ ስርዓት በካፒታል ሆቴል ተካሂዷል።

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-21