የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ሀገራቸው በሶሪያ ላይ አዲስ ወታደራዊ ጥቃት ለመፈፀም የያዘችው ውጥን የፀጥታ ስጋቶቿ እስካልተፈቱ ድረስ በአጀንዳነት ይቀጥላል አሉ።
ተርኪዬ በሰሜን ምስራቅ ሶሪያ የኩርድ ታጣቂዎች ላይ አዲስ ጥቃት እንደምትፈጽም ያስታወቁት ኤርዶጋን ከሁለት ቀናት በፊት ከሩሲያ እና ከኢራን አቻዎቻቸው ጋር በሶሪያ ጉዳይ ላይ መመካከራቸው አይዘነጋም።
በንግግራቸውም ቱርክ በኩርድ ታጣቂዎች ላይ ለምታካሄደው አዲሱ ዘመቻ ድጋፍ ጠይቃለች።ኤርዶጋን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሶስቱ ሀገራት ዋይፒጂን በሚመለከት ከተርኪዬ ጋር ወጥ አቋም አላቸው ብለዋል።
ዋይፒጂ ነፃ የኩርድ ግዛት እንዲኖር ለአስርት አመታት የዘለቀ የትጥቅ ዘመቻ ያደረገ ታጣቂ ቡድን ነው
በመቅደስ እንዳለ
2022-07-21
