ሀገሬ ቲቪ

አሜሪካ ከሀምሳ የአፍሪካ መሪዎች ጋር ልትወያይ ነው

ጆ ባይደን በጎርጎሮሳውያኑ ታህሳስ አጋማሽ ላይ የአሜሪካ-አፍሪካ ስብሰባ ለሶስት ቀናት እንደሚካሔድ አስታወቁ።

50 የአፍሪካ መሪዎች በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከፕሬዝዳንት ባይደን ጋር በመሆን የምግብ ዋስትና የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችን ከረሃብ ለመታደግ ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ለኢትዮጵያ፣ኬንያ እና ሶማሊያ የ1ነጥብ3 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ ሰጥቻለሁ ማለቱን አልጀዚራ ጽፏል ።

በመቅደስ እንዳለ
2022-07-21