ሀገሬ ቲቪ

“በኦሮሚያ የተፈጸመው የንጹኃን ሞት በገለልተኛ አካል ይመርመር” ፦ አምነስቲ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኦሮሚያ ክልል ከ400 በላይ የሚሆኑ የአማራ ብሔር ዜጎች ላይ የተፈፀመው ግድያ መንግሥት ምርመራ ያካሄድበት አለ።

የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ የአምነስቲ ዳይሬክተር ዴፕሮሴ ሙቼና በሰጡት መግለጫ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እጅ ተጠያቂ ነው በተባለበት እና በቶሌ የተፈፀመው ዘግናኝ ግድያ ወንጀለኞቹ ለሰው ህይወት ያላቸውን ንቀት ያሳያል ብለዋል።

ከ450 በላይ ዜጎች መገደላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ለድርጅቱ ነግርውታል። የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ቢልለኔ ስዩም ከዚህ ቀደም በጥቃቱ 338 ዜጎች ህይወታቸው እንዳለፈ መግለጻቸው አይዘነጋም ።ከጥቃት የተረፉ ዜጎች አናግሬያለሁ የሚለው አምነስቲ ጥቃቱ የተፈጸመው በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ነው ይላል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-07-21