ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአስቸጋሪ የጤና ሁኔታ መቆየታቸውን ጠቅሰው ከሀገር ውጪ ለመታከም ማሰባቸውን ገለጹ።
በተቻለ መጠን የተለየ ችግር ካልገጠማቸው ከአንድ ወር ባላነሰ ጊዜ ሕክምናቸውን አጠናቀው ወደ በመንበረ ፕትርክናቸው እንደሚመለሱ ተናግረዋል።
የዐይን ሕክምና ጨምሮ ሙሉ ሕክምናቸውን አጠናቀው አስኪመለሱ አባቶችና ምእመናን በጸሎት ያስቡኝ ያሉት ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቤተክርስቲያን ክብር አስጠብቀው ሥራቸውን በኃላፊነት እንዲያከናውኑ አደራ ብለዋል፡፡
በመቅደስ እንዳለ
2022-07-22
