ቺሊ የ35 ዓመት ዕድሜ ያለውን ወጣት ፐሬዚዳንቴ ሁን መርጬሃለው ስትል ሾማዋለች። አዲሱ የቺሊ ፕሬዝዳንት ገብርኤል ቦሪክ ቀደም ባለው ግዜ የተማሪዎች አክቲቪስት አሊያም የፖለቲካ አንቂ ነበር። ወጣቱ ፕሬዝዳንት በሀገሪቱ ተካሂዶ በነበረው የፀረ-መንግስት ተቃውሞ ወቅት በእነበረው እቋም ዝናን አትርፏል። ይህ ዝናም ይመስላል ለቀድሞ የፖለቲካ አክቲቪስት ሀገሪቱን በፕሬዘዳንትነት እንዲመራት አመኔታ አስገኝቶለታል። በሀገሪቱ በተደረገው ምርጫ ከተሰጠው 99 በመቶ ድምጽ 56 በመቶውን በማግኘት የመሪነት ዕርካቡን ጨብጧል። ተቀናቃኙ ጆሴ አንቶኒዮ ካስት 44 በመቶ ድምጽ በማግኘት በቀድሞው የፖለቲካ አክቲቪስት ተረትቷል። ካስት መረታቱን በመቀበል የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት ለገብርኤል ቦሪክ ልኮለታል። ታዲያ አዲሱ ፕሬዝዳንት ቦሪክ ከተሰናባቹ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሴባስቲያን ፒኔራ ጋር በበይነ መረብ መክረዋል። ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ለአዲሱ መንግስት አስፈላጊውን እገዛ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆናቸውን ሰምቻለሁ ሲል አልጀዚራ ዘግቧል። በዕድሜ ትንሹ ፕሬዝዳንት አጠር ላሉ ደቂቃዎች በቴሌቭዥን ባደረጉት ንግግር፤ “አሁን የቺሊ ፕሬዝዳንት ሆኛለሁ ይህን ታላቅ ፈተና ለመወጣት የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ” ሲሉም ለህዝባቸው ቃል ገብተዋል።
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-20
