ሀገሬ ቲቪ

የሩሲያ እና ዩክሬን የእህል የወጪ ንግድ ስምምነት ተፈራረሙ

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በዓለም የምግብ ምርቶች ላይ እጥረት በመከሰቱ ሁሉም የዓለም ህዝቦች ደረጃው ይለያይ እንጂ እጥረቱ ተጋላጭ ሆነዋል።

ሁለቱ አገሮች የስንዴ፤ የቅባት እህሎችንና ማዳበሪያ ለዓለም ገበያ በማቅረብ ይታወቃሉ። በጦርነቱ መከንያት ከሁለቱም ሃገራት የሚቀርበው ምርት በመቋረጡ ታዳጊ ሀገራት ለምግብ እህል እጥረት መጋለጣቸውን የሚውጡ መረጃዎች ያመለከታሉ።

ሩሲያ በተጣለባት ማዕቀብ፤ ዩክሬን ደግሞ በሩሲያ ወደቦቿ ስለተዘጉና ስለተከበቡ ምርታቸውን ወደ ውጭ መላክ አልቻሉም።

ዩክሬን በወደቦቿ ተከማችቶ የሚገኘውን ስንዴ ለገበያ ማቀርብ ብትችል አንዱ የችግሩ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል።

ይህ እንዲሆን ደግሞ በዩክሬን ወደቦች ተከማችቶ ያለው እህል በሰላም ወደ ውጭ እንዲላክ ሩሲያ መፍቀድ ይኖርባታል በሚል በርካቶች ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

ሩሲያ ዩክሬን በወደቦቿ ዳርቻ ያጠመደቻቸውን ፈንጅዎች እንድታጸዳና ሩሲያም እህሏን ለገበያ ለማቅረብ እንድትችል ማዕቀቡ እንዲነሳ መጠየቋ ተገልጿል።

ዩክሬን ግን በወደቦቿ ዳርቻ ያጠመደቻቸውን ፈንጂዎች ካጸዳች፤ ለሩሲያ ጥቃት እጋለጣለሁ በማለት ዋስትና እንደምትሻ ትናገራለች፡፡

የህ በዚሀ ሁኔታ እነዳለ ዩክሬንና ሩሲያ የእህል የወጪ ንግድ ስምምነት ዛሬ ሊፈራረሙ እንደሆነ የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶጋን ይህንን ብለዋል።

“ሩሲያ፣ ዩክሬን እና ተርኪዬ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈውን ይህን ስምምነት ወደ ውጭ የሚላኩ የእህል ምርቶችን ለመልቀቅ ፊርማ ያካሂዳሉ። ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ላለው የዓለም የምግብ መናር መፍትሄ ይሆናል።”

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከዩክሬን ወደቦች የሚወጡ መርከቦች ያለስጋት እንዲያልፉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ስምምነቱ ከኦዴሳ እህል ጭነው የሚወጡ መርከቦችን ደህንነት መጠበቅን ጨምሮ፣ ዋና ዋና ጉዳዮችን ያካትታል።

በሩሲያ የባሕር ኃይል እገዳ ምክንያት 20 ሚሊዮን ቶን የሚሆን የእህል ምርት በዩክሬን ውስጥ ለአደጋ ተጋርጦ እንደሚገኝ ታውቋል።

ከዚህ ቀደም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዩክሬን በሚገኘው የጥቁር ባሕር ወደብ ያለውን የእህል ምርት ወደ ውጪ ኤክስፖርት እንዲደረግ መጠየቁ አይዘነጋም ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ሃሙስ ወደ ኢስታንቡል ያመሩት በዶልማባቼ ቤተመንግስት በስምምነቱ ለመታደም ነው ተብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት በጦርነቱ ምክንያት በዩክሬን ጥቁር ባህር ወደቦች ላይ የከረመውን የእህል ክምችት ዩክሬን ወደ ውጭ ለመላክ የሚያስችላትን እቅድ እንደነደፈ ተሰምቷል።

ባሳለፍነው ሳምንት ሁለቱ ወገኖች በኢስታንቡል ተገናኝተው በእቅዱ ላይ ጊዜያዊ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የቱርክ ባለስልጣናት አስታውሰዋል።

መርከቦቹ ወደ ጥቁር ባህር ወደቦች ሲወጡ እና ሲደርሱ የጋራ ቁጥጥር እንደሚደረግ እና የመተላለፊያ መንገዶችን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መላ እንደሚዘየድም ባለስልጣናቱ ገልጸዋል።

ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች የማስተባበሪያ ማዕከል በኢስታንቡል ውስጥ የሚቋቋም ሲሆን የዩኤን፣ የቱርክ፣ የሩሲያ እና የዩክሬን ባለስልጣናት ሚና እንደሚኖራቸውም ተነግሯል።

አሜሪካ በበኩሏ ስምምነቱን በደስታ እንደምትቀበል ገልጻ፤ ሩሲያ ስምምነቱን እንድታከበር ትኩርት ስጥታ እንደምትሰራ አስታውቃለች ።

የሩሲያ እና የዩክሬን ባለስልጣናት በእህል ጭነቱ መዘጋት እርስ በእርሳቸው ሲወቃቀሱ መቆየታቸውን አልጀዚራ ጽፏል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-07-22