ሀገሬ ቲቪ

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ጉብኝት

ሩሲያ ከምዕራብ ሀገራት ከተጣለባት ማዕቀቦች እና ዲፕሎማሲያዊ መገለል ለመውጣት እየጣረች ነው ።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሰርጌ ላቭሮቭ በአራት የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እንደሚያደርጉ በትናገሩት መሠረት የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በይፋ በሰሜን አፍሪካቷ ግብጽ አንድ ብለው ጀምረዋል።

ላቭሮቭ በካይሮ ጉብኝታቸው ግብፅን የእህል አቅርቦት ጉዳይ ሀሳብ አይግባሽ ብለዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ከቀናት በፊት ስምምነት ላይ የተደረሰው የሩሲያና የዩክሬን የእህል የወጪ ንግድን ታሳቢ አድርገው ነው።

ሩሲያ ከጎጎሮሳውያኑ የካቲት ወር ጀምሮ ለግብፅ ስንዴ በማቅረብ ለመንግሥትም ሆነ ለግሉ ዘርፍ በመሸጥ ላይ ቆይታለች።

ግብፅ ከዓለም ቀዳሚ ስንዴ አስገቢ ስትሆን ባለፈው ዓመት 80 በመቶ የሚሆነውን ከሩሲያ እና ከዩክሬን አስመጪዎች ሽምታለች።

በሁለቱ እህል ላኪዎች መካከል ለወራት የዘለቀው ውዝግብ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሸቀጦች ዋጋ ንረት በማባባስ በግብፅ ላይ የገንዘብ ቀውስ በማስከተሉ ግብጽ የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት አይ.ኤም.ኤፍ ድጋፍ እስከመጠየቅ ደርሳለች።

የግብጽ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነው የቱሪዝሙ ዘርፍ በከፍተኛ ሁኔታ ተዳክሟል።

ሩሲያን ከጨዋታ ውጪ ለማድረግ ከሞከሩት ከምዕራባውያን ኃያላን ጋር ባላት የጠበቀ ግንኙነት መካከል ነው ሆድና ጀርባ ሆነው የቆዩት ሲል አልጀዚራ ጽፏል ።

የምዕራቡ ዓለም ኤምባሲዎች ከላቭሮቭ ጉብኝት በፊት ግብፅን እና የአረብ ሊግ ውይይት እንዳያደርጉ ሲወተውቱ ነበር።

ላቭሮቭ ከግብፅ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “በአገራቸን ላይ የተጣለው ማዕቀብ በዓለም የምግብ ዋስትና ላይ ተጸእኖ እያሳደረ ነው ።

የምዕራባውያን ሀገራት ግን እውነታው አይዋጥላቸውም። ምዕራባውያን አገራት የበላይነታቸውን በሌሎች ላይ ለመጫን እየሞከሩ ነው።

በወጪ ንግዱ ከግብጽ ጋር አንድ ላይ መስራት በምንችልባቸው ጉዳዮች አውርተናል።በሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል ተጨማሪ ግንኙነቶች እንዳደርጋለን“ሲሉ ተናግረዋል።

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሚሊዮን ቶን የሚቆጠሩ እህሎች በዩክሬን ወደቦች ውስጥ ተይዘዋል,።

ሩሲያ፣ ዩክሬን፣ ተርኪዬ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አርብ ዕለት የዩክሬይንን ስንዴ በባህር ወደ ውጭ ለመላክ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ከስምምነቱ ከሰዓታት በኋላ ሩሲያ በዩክሬኑ ኦዴሳ ወደብ ላይ ጥቃት መሰንዘሯ ሩሲያ ለስምምነቱ ያለት ቁርጠኝነት ላይ ጥያቄ የሚፈጥር ነው ተብሏል።

በርካቶች ስምምነቱ ላይሳካ እንደሚችል ገመታቸውን እየገለፁ ሲሆን፤ በጥቃቱ ዙሪያ ሞስኮ ንግግር ከማድረግ ተቆጠባለች።

ዩክሬን በበኩሏ ለገበያ የሚቀርበውን እህል ለመላክ ዝግጅቷን ቀጥላለች። ከ17 ሀገራት የተውጣጡ 70 መረከቦች ከሞላ ጎደል ታግተዋል በሚያስኝ ደረጃ እዚያው ቆመው ይገኛሉ።

በአጋጣሚ ለግብፅ ምግብ ያድርሳል ተብሎ የሚታስብ አንድ መርከብ በቦምብ ፈንዳታ ሥጋት ምከንያት በዩክሬን ወደብ ይገኛል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ከግብጽ ጉብኝታቸው ቀጥለው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ተነግሯል።

በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከአፍሪካ ህብረት ተወካዮች፣ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት እና ከተለያዩ ሀገራት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር ይመክራሉ።

ላቭሮቭ በኡጋንዳ እና በዲሞከራቲክ ኮንጎም የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-07-25