ሀገሬ ቲቪ

የሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የተማሪዎችን ምረቃ

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስተማሩዋቸውን ተማሪዎች የሚያስመርቁበት ወር ላይ እንገኛለን። በርካታ የትምህርት ተቋማትም በዚህ ወር ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል እያስመረቁም ይገኛሉ።

ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ የእውቅና ፈቃድ ያገኘውና በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎችን እያስተማረ የሚገኘው ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅም በተለያዩ የትምሕርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከ2006ዓ.ም ጀምሮ እስከ2014 ዓ.ም በአጠቃላይ ወደ 2ሺህ የሚጠጉተማሪዎችን አስመርቋል።

የትምህርት ተቋሙ ሰፊ የማስተማር አቅም ቢኖረውም ለትምሕርት ጥራት ሲባል ውስን ተማሪዎችን ብቻ እየተቀበለ እንደሚያስተምር የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተረፈ ፈዬራ ነግረውናል።

ከዚህ በተጨማሪ ዩኒቨርስቲ ኮሌጁ ከፍለው መማር ለማይችሉ ተማሪዎች የስኮላርሺፕ ዕድል በመስጠት በተቋሙ ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል።

ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ጋር በመቀናጀት ለመማር አቅም የሌላቸውን ተማሪዎች በመለየት እና በማወዳደር ይህን ዕድል ይሰጣል።

ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በ2014 ዓ.ም ከ 3 መቶ በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የትምሕርት መስኮች አሰልጥኖ አስመርቋል።

ከተቋማት ጋር በመቀናጀትም እነዚህ ተማሪዎች ዘላቂ የሥራ ዕድል እንዲያገኙ እያደረገ ስለመኾኑ ሰምተናል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-07-25