ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደረሰበት ኪሳራ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ130 ሚሊየን ብር በላይ ኪሳራ ደርሶብኛል አለ። ይህ ኪሳራ ሊደርስ የቻለው በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማትና በኃይል ስርቆት መኾኑ ተሰምቷል።

ከዚህ ጋር የተያያዙ ተቋሙ 7 መቶ 59 የወንጀል ክሶችን የመሠርተ ሲሆን፣ በ36 መዝገቦች ላይ ፍርድ ቤት ባስተላለፈው የመጨረሻ ዉሳኔ ወንጀሉን በፈጸሙ 64 ተከሳሾች ከ6 ወር እስከ 12 ዓመት ጽኑ እስራት ተወስኖባቸዋል።

በሌላ በኩል ውዝፍ የኃይል ፍጆታ ሒሳብ ካለባቸው ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች 177 ሚሊየን ብር በላይ የህግ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ማስከፈል መቻሉ ተጠቅሷል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-07-25