
በጊኒ ከኢቦላ ቫይረስ ጋር ተዛምዶ ያለው ማርበርግ የተሰኘ ቫይረስ መከሰቱ ተነገረ። የሀገሪቱ የጤና አገልግሎት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ማገኘቱን አስታውቋል።
አሻንቲ በተባለው ግዛት በቫይረሱ የተያዙ ኹለት ሰዎች ከተገኙ እና ወደ ለይቶ ማቆያ ከገቡ በኋላ ንክኪ የነበራቸው 98 ስዎች መለየታቸው ተነግሯል።
ተቅማጥ፣ ትኩሳት፣ የማቅለሽለሽ ስሜትና ማስመለስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው የሚያሳያቸው የሕመም ዓይነቶች ናቸው ተብሏል።
ማርበርግ ቫይረስ ከሌሊት ወፎች እንደመጣ ይገመታል። አሁን ላይ ለቫይረሱ ኹነኛ ክትባት ባለመኖሩ ሰዎች የእንስሣት ተዋጻኦዎችን ከመመገብ እንዲቆጠቡ የጊኒ የጤና ሹማምንቶች አሳስበዋል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-07-25