ሀገሬ ቲቪ

የደቡብ አፍሪካ ማዕከላዊ ባንክ የወለድ ምጣኔን ማሳደግ

የደቡብ አፍሪካ ማዕከላዊ ባንክ የወለድ ምጣኔውን አሳደገ። ማዕከላዊ ባንኩ የወለድ ምጣኔውን ያሳደገው ወደ 5 ነጥብ 5 በመቶ ነው።

በ10 ዓመቱ ውስጥ ከፍተኛው ነው የተባለለት የወለድ ምጣኔ ከፍ ማለት የሀገሪቱን የዋጋ ግሽበት ለመቀነስ ያለመ ስለመሆኑ ተገልጿል።

የደቡብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ከ1 ነጥብ 7 በመቶ በመሻሻል የ2 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል ተብሎም ይጠበቃል።

በአብርሃም በለጠ
2022-07-25