ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ ባለውለታ ህልፈት

በ1977 ዓ.ም በነበረው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከደረሱት መካከል የሆነው የጥበብ ሰው ኬን ክራገን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ኬን ክራገን በ1977 ዓ.ም በኢትዮጵያ ውስጥ ተከስቶ ለነበረው ድርቅ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማሰባሰብ የተዘጋጀውን 'We Are The Wolrd' የተሰኘውን ህብረ ዝማሬ ካቀናበሩት፣ ከመሩት እና ለአድማጭ ካቀረቡት የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች አንዱ ነበር። ህብረ ዝማሬው በተመሳሳይ ሰዓት በመላው ዓለም በ30 ሺሕ የሬድዮ ጣቢያዎች ላይ ተሰራጭቶ ሚሊዮኖችን አንቅቷል። ክራገን ከነ ሎዮኔል ሪቼ፣ ኬኒ ሮጀርስ ፣ ማይክል ጃክሰን እና ሌሎችም የዓለማችን አንጋፋ የጥበብ ሰዎች ጋር በመሆን የሰሩት ' We Are The World ' የተሰኘው ሙዚቃ በወቅቱ የዚያን ዓመት የኤሚ አዋርድን አሸንፏል። ክራገን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም ሜዳልያ ተሸላሚም ነበር። ጃክሰን እና ሪቺ በጋራ የፃፉት "We are the World" በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቅጂዎችን በመሸጥ የዓመቱን ሪከርድ መስበርም ችሏል። በተጨማሪምለ USA For Africa 64 ሚሊዮን ዶላር በማሰባሰብ ብዙ የግራሚ ሽልማቶችን አሸንፏል። ፕሮድዩሰር፣ ስራ አስኪያጅ እና በጎ አድራጊው ክራገን በ85 ዓመታቸው በአሜሪካ ሎስ አጀለስ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እንዳረፉ አሶሼት ፕሬስ ዘግቧል።

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-20