ዩፎ የሚለው ቃል ያልተረጋገጡና ምንነታቸው ያልታውቁ በራሪ አካላት መጠሪያ ነው። ግኡዝ በራሪ አካላቱ ያለ ጪስ ማውጫ ከቴክኖሎጂ በተቃረነ መልኩ ፍጥነት ይጓዛሉ ይላሉ ።
ስለ እነዚህ ግኡዝ በራሪ አካላት ሲነሳ በሳይንሳዊ አጠራራቸው ኤሊያን የሚባሉት ፍጡራን አብረው ይነሳሉ።
ኤሊያኖች ከእኛ አለም ወጭ ይኑሩ አይኑሩ የተረጋገጠ ነገረ ባይኖርም፣ ወደ ምድር መተው እየሰለሉ ነው በሚል በርካቶች ግምታቸውን ይስቀምጣሉ።
የአሜሪካ መንግሥት በአውሮፕላን አብራሪዎች ታይተዋል በሚል በተደጋጋሚ ሲገለጹ ስለከረሙ ምንነታቸው ስላልታወቀ በራሪ አካላት ወይም ዩፎዎች ጉዳይ ዝምታውን መረጦ ቆይቷል።
በርካታ በራሪ ነገሮች መደበኛ ባልሆነ ሁኔታ በሰማይ ላይ መታየታቸውን ተከትሎ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) የ ይፎ ምርመራ ቢሮ በይፋ እየከፈተኩ እንደሆነ እወቁልኝ ብሏል።
አሜሪካ የዩፎዎች ጉዳይ ያሳሰባት ትመስላለች።
የAll-domain Anomaly Resolution Office (AARO) የተሰኘው የ አዲሱ ቢሮ ዋና ተልእኮ የበራሪ አካላትን መለየት፣ መተንተን በዝርዝር ማቅረብና የበራሪ አካላቱን ተፈጥሮ ከየት እንደመጡ ተጨማሪ መረጃን ማሰባሰብ ነው።
በአየር በረራ ላይ ግልጽ የሆነ የደኅንነት ስጋት የሚያስከትሉ እና ምናልባትም ለአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት ፈተና ሊሆኑ እንደሚችሉ ሊይቭ ሳይንስ ጽፏል።
እስካሁን ግልጽ ማስረጃ ያልተገኘላቸው እነዚህን ያልታወቁ በራሪ አካላት ተመለከትን የሚሉ አሜሪካያኑ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም።
የአሜሪካ ሹማምንት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ እንደተናገሩት ከሆነ በራሪ አካላቱ እንግዳ ፍጥረቶች ወይም ኤሊያን ሊሆኑ ይችላሉ ይህም ካልሆኑ እንደ ሩሲያ ወይም ቻይና ካሉ የአሜሪካ ተቀናቃኝ አገራት የተላኩ ቴክኖሎጂዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
የአሜሪካን ባህር ኃይል በሦስት የተለያዩ ወቅቶች ቀርፆ ያስቀመጣቸው ምንነታቸው ያልታወቁ ነገሮች በከፍተኛ ፍጥነት ሲበሩ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ይፋ አድርጎ ነበር። ይህንንም ተከትሎ የአሜሪካ መንስግስት በባለፉት ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በዩፎ ላይ ያለው ፍላጎት እንደ አዲስ ታድሷል።
የአሜሪካ የባሕር ሃይል ተንቀሳቃሽ ምስሎቹን በሚያዝያ 2020 በይፋ አረጋግጦ ይፋ አድርጎ ነበር ።ነገር ግን ምስጢራዊ ነገሮች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ምንም አይነት ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል።
በጎሮጎሮሳውያኑ 2020 የዩኤስ ሴኔት ላልታወቁ በራሪ አካላት የቀረቡ ሪፖርቶችን የሚመረምር ግብረ ኃይል አቋቁሞ ነበር። በጎጎሮሳውያኑ ሰኔ 2021፣ የፔንታጎን የባህር ኃይል አብራሪዎች ከ140 በላይ የዩፎ እይታዎችን ሪፖርት አድርገዋል።
አዲሱ ቢሮ የሚተዳደረው በአሜሪካ የመከላከያ ኢንተለጀንስ ኤጀንሲ የሚሳኤል እና የጠፈር መረጃ ማዕከል ዋና ሳይንቲስት ሾን ኤም.ነው ተብሏል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-07-26
