ሀገሬ ቲቪ

በሰሜኑ ጦርነት 79 ቅርሶች ላይ ጉዳት ደረሰ

በሰሜኑ ጦርነት 68 ተንቀሳቃሽ እና 11 ቋሚ ቅርሶች ላይ ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ።

ሰሜን ጎንደር እና ሰቆጣ አካባቢ በጸጥታ ምክንያት ያልተዳረሱ ቦታዎች በመሆናቸው አደጋ የደረሰባቸው የቅርሶች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ተሰምቷል።

ሙዚየም ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ፣ አብያተ ክርስቲያናት፣ መስጊዶች እና ጉዳት የደረሰባቸው ቅርሶች በቋሚነት እስኪጠገኑ፣ ፈጣን ጥገና ተደርጎላቸው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ለማስቻል ከዓለም ባንክ 159 ሺሕ ዶላር ተገኝቷል።

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-25