ሀገሬ ቲቪ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽህፈት ቤት ተዘረፈ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚገኘው ሰላም አስከባሪ ቢሮዬ ተዘርፏል አለ።

ለተቃውሞ የወጡ ከ100 በላይ የሚሆኑ ዜጎች በኮንጎ ያለው የሰላም አስከባሪ ሊጠብቀን ስላልቻለ ከሀገር ለቆ ይዉጣ በሚል ዝርፊያ ፈጽመዋል ሲል ሮይተርስ ጽፏል።

እነዚህ ዜጎች ወደ ፅሀፈት ቤቱ የሚወስደውን መንገድ በድንጋይ በመዝጋትና እሳት በማንደድ ዝርፊያውን ፈጽመዋል። መጋዘኖች በመግባትም ዝርፊያ የፈፀሙ ሲሆን በገንዘብ ምን ያህል እንደሚተመን መረጃው ያለው ነገር የለም።

በመቅደስ እንዳለ
2022-07-26