ቴክኖሎጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ ራሱን እያዘመነ የሰው ልጆችን ህይወት አቅላይ ሆኗል ። በዛው ልክ ደግሞ በሰው ልጆች ህይወት ላይ አንዳንድ ጉዳት ማድረሱም የማይካድ ሃቅ ነው ።
ዓለማችን አሁን ላይ በደረሰችበት ደረጃ የሰዎችን ስራ ያግዛሉ ያሏቸውን አንድ አጋዥ ነገር ፈጥረዋል። ስማቸውም ሮቦት ይባላል። እነዚህ ሮቦቶች ከሳሎን እስከጓዳ የሰዎችን ስራ ማቅለል ብቻም ሳይሆን አጋዥም ወደ መሆን ተሻግረዋል።
ስለ ሮቦት ያነሳንላቹ ያለምክንት አይደልም በሩሲያ ሞስኮ ከተማ ውስጥ በርካታ ሰዎች የታደሙበት ልዩ የ ቼዝ ውድድር ተዘጋጅትዋል ።
ውድድሩ እየተኪያሄደ የሚገኘው በ አንድ የሰባት አመት ልጅ እና በ ሮቦት መካከል ነው ። በሮቦቱና በተቀናቃኙ መካከል የሚደረገው ፍልሚያ በበርካታ ሰዎች ድጋፍ ታጅቦ ቀጥሏል።
ግማሹ ለሮቦቱ ግማሹ ደግሞ ለ 7 ዐመቱ ታዳጊ ልጅ ድጋፋቸውን እየሰጡ ነው ። ታዲያ በድንገት አንድ ነገር ተፈጠረ ሮቦቱ የተቀናቃኙን ጣት አጥብቆ ይዞ አለቅም አለ ።
በ አካባቢው ለድጋፍ የመጡ ሰዎች ተረባርበው የልጁን ጣት ሊያስለቅቁ ቢሞክሩም ያ ሮቦት ግን አሻፈረኝ አለ ። በሰዎቹና በሮቦቱ መካከል በተደረገው እልህ አስጨራሽ ግብ ግብ የልጁ ጣት ነጻ ቢወጣም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ነበር ።
የሞስኮ የቼዝ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የሆኑት ሰርጌይ ላዛሬቭ ለ ሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ሮቦቱ ከዚህ በፊት በርካታ ጨዋታዎችን አድርጎ ያውቃል ነገር ግን እንዲህ አይነት ነገር ማንም ሰው ላይ አድርሶ አያውቅም በልጁ ጣት ላይ ባደረሰው ከፍተኛ ጉዳት ሁላችንም አዝነናል ከዚህ በኋላ በጨዋታዎች እንዳይሳተፍም ወስነናል ሲሉ ተናግረዋል ።
ስፖርተኞች ሲያጠፉ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ይህን ሮቦትም ፌዴሬሽኑ ካሁን በኋላ እንዳላይህ ብሎታል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-07-26
