ለገና በዓል ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ጥሪ የተደረገላቸው ዲያስፖራዎች የማረፊያ ችግር እንዳያጋጥማቸው ህብረተሰቡ ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ። በከተማዋ ከ20ሺሕ ያልበለጠ አልጋ እንዳለ እና ይህም ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገቡት ዲያስፖራዎች በቂ እንደማይሆን የአ.አ ባህል ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ሂሩት ካሳ(ዶ/ር) ተናግረዋል። ይህን ችግር ለመቅረፍ ታዲያ አፓርትመንት ቪላቤት የእንግድዳ ማረፊያ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በየክፍለ ከተማቸው በሚገኙ የባህል እና ቱሪዝም ጽ/ቤት በማስመዝገብ ለነዚሁ ዲያፖራዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለኪራይ ዝግጁ እንዲያደርጉ ሃላፊዋ ጠይቀዋል። አሁን ላይ በከተማዋ ያሉ ሆቴሎች እና አገልግሎት ሠጪ ተቋማት 30 በመቶ የዋጋ ቅናሽ በማድርግ ዲያስፖራዎቹን ለመቀበል ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው ተነግሯል። በሀገሪቱ ያሉ የተለያዩ የቱሪስት መስህቦች ለጉብኝት ዝግጁ የተደረጉ ሲሆን አስጎብኚ ተቋማትም የዝግጅት ስራቸውን ማጠናቀቃቸው ተጠቁሟል ከዚያ ባሻገር ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ ዲያስፖራዎች በሀገር የተመረቱ የተለያዩ ምርቶችን የሚሸምቱበት ባዛር ተዘጋጅቷል። የተለያዩ ኪነጥበባዊ መርሀግብሮች እና የሙዚቃ ኮንሰርት መዘጋጀቱም ተነግሯል። ሁሉም ዜጋ ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ ዱያስፖራዎችን የእንኳን ደህና መጣችሁ የተለመደውን መልካም አቀባበል እንዲያደርግላቸው ኃላፊዋ በመግለጫቸው ጠይቀዋል።
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-21
