ሀገሬ ቲቪ

የሱማሊያና የግብጽ ውይይት

አዲሱ የሱማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሳን ሼክ ማህሙድ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት ቀጥለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ሰባተኛ የውጪ ጉብኝታቸውን ወደ ግብጽ በማድረግ ከፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ ጋር መምከራቸው ተሰምቷል።

በሀገራቱ መካከል ያሉትን የጋራ ፕሮጀክቶች ዕድገት መገምገማቸውን እና ሶማሊያ ምጣኔ ሀብቷን ለማልማት የምታደርገውን ጥረት ለማጠናከር ተስማምተናል ሲሉ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታ አልሲሲ ከውይይታቸው በኋላ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ስላለው የደህንነት ሁኔታም ውይይት አድርገናል ብለዋል። የመሪዎቹ ንግግር በቀይ ባሕር ያለውን የደህንነት ጉዳይ የተመለከተ እንደነበርም ሲጂቲኤን ዘግቧል።

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-26