ጋዝፕሮም የተሰኘው የሩሲያ ግዙፍ የጋዝ አምራች ተቋም በጋዝ ማስተላለፊያ ቱቦ ወደ አውሮፓ የምልከውን የጋዝ መጠንን በ20 በመቶ ቀንሻለሁ ብሏል።
ይህ ውሳኔ የአውሮፓ ሀገራት ለዩክሬን ያደላ ውሳኔዎችን እና ድጋፎችን በማድረጋቸው የመጣ ነው ተብሏል። ሩሲያ በበኩሏ የጋዝ ማስተላለፊው ትቦ ላይ ጥገና መደረግ ስላለበት ነው የሚል ምክንያትን አቅርባለች።
በዚህ ወር ይኽው መስመር ለጥገና ተብሎ ለ10 ቀናት ሙሉ ለሙሉ ተዘግቶ እንደነበር የቢቢሲ ዘገባ አስታውሷል። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው በአውሮፓ ላይ የታወጀ የጋዝ ጦርነት ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-26
