ሀገሬ ቲቪ

ይቅርታ የጠየቁት ፕሬዝዳንት

የአፍሪካው ቼ ጉቬራ በመባል ይታወቃል በሙሉ ስሙ ቶማስ ኢሲዶር ኖኤል ሳንካራ በፀረ-ኢምፔሪያሊስት አቋሙ፣ ከምዝበራ በጸዳዉ አኗኗሩ ለብዙዎች ጀግና ነው በተለይ በእናት ሀገሩ ቡርኪናፋሶ እና በአፍሪካውያን ዘንድ ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ቀደምት የነጻነት ታጋዮች ተርታ ይመደባል ገና በ33 ዓመቱ ስልጣን የተቆጣጠረው የማርክሲስት አብዮተኛ ሳንካራ በሙስና ላይ ዘመቻ በማካሄድ ከፍተኛ የትምህርት እና የጤና መሰረተ ልማት ላይ መስራቱ እስከዛሬም ስሙ በጥሩ እንዲነሳ ምክንያት ሆኖል፡፡

ደግ ሰው አይቆይም እንደሚሉት የታላላቆች ንግግር ታዲያ ሳነካራ በ1979 ዓ.ም በተካሄደዉ መፈንቅለ መንግሥት ህይወቱን አጣ፡፡ ቡርኪናፋሶ ከራሷ አልፎ ለአፍሪካ ይተርፋል ያለችው እና ተስፋ የጣለችበት ይህ ወጣት እንደቀልድ ተሰናበተ።

ታዲያ በወቅቱ የቡርኪናፋሶ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ብሌዝ ኮምፓኦሬ ደግሞ በግድያው ላይ በነበራቸው ሚና ሲወቀሱና ገዳይ ሲባሉ ኖረዋል።

ኮምፓኦሬ ከ27 ዓመታት የስልጣን ቆይታ በኋላ በህዝባዊ አመጽ ከስልጣን የተወገዱ ሲሆን ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በጎረቤት ሀገር አይቮሪ ኮስት በስደት እየኖሩ ነው።

ባሳለፈንው ሚያዝያ ኮምፓኦሬ በግድያው ላይ እጃቸው አለበት በሚል በሌሉበት የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

ታዲያ ፕሬዝዳንቱ ከ 27 ዓመታት በኋላ ካሉበት ጎረቤት ሀገር አይቮሪኮስት ድምጻቸውን አሰምተዋል። በተካሄደዉ መፈንቅለ መንግሥት እና ግድያ በተፈጸመበት ቶማስ ሳንካራ ዙሪያ ቤተሰቦቹን ይቅርታ አድርጉልኝ ሲሉ ተማጽነዋል። የቶማስ ሳንካራ ሞትን አደጋ ነዉ ሲሉም አስተባብለዋል።

የቡርኪናፋሶ ህዝብ በስልጣን ዘመኔ ለፈፀምኳቸው ድርጊቶች ሁሉ እንዲሁም ለወንድሜ እና ለጓደኛዬ ቶማስ ኢሲዶር ኖኤል ሳንካራ ቤተሰብ ይቅርታ አድርጉልኝ ሲሉ ዝቅ ብለዋል።

በሀገር መሪነት ስልጣን በያዝኩበት ጊዜ ሁሉ ተጎጂዎች ላጋጠሟቸው ስቃይ እና መከራ ከልቤ አዝናለሁ እናም ቤተሰቦቻቸው ይቅርታ እንዲያደርጉልኝ እጠይቃለሁ።

በአያቶቻችን ምድር ላይ የጋራ እጣ ፈንታችንን እንደገና ለመገንባት ከአሁን በኋላ ወደፊት እንደምንሄድ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-27