ሀገሬ ቲቪ

አገልግሎት የጀመረው ሀይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ለሀይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። ሆስፒታሉ ድጋፍ ያደረገው የመድሀኒት ግብዓቶች እና የህክምና ቁሳቁስ ከ 7ነጥብ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ነው፡፡ ከድጋፉ ባሻገር ሆስፒታሉ በድንገተኛ ክፍል ህክምና፣በእናቶችና ህፃናት ህክምና፣በማዋለድ አገልግሎት፣በተመላላሽና ተኝቶ ህክምና አገልግሎት ፣በላብላቶሪ እና ፋርማሲ አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ያሬድ አግደው ለአመራሩና ጤና ባለሙያው አስረክበዋል። የህወሓት ሀይል ውድመት ያደረሰበት የሀይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር አደርጋለሁ ሲል ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ሃላፊነቱን ወስዷል ከዚህ በተጨማሪም ከሆስፒታሉ ባለሙያዎች እና ከረጅ ድርጅቶች የተሰበሰቡ ግምታቸው ከ1ሚልየን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብና የአልባሳት እንዲሁም የቁሳቁስ ድጋፎችን ለአካባቢው ማህበረሰብ መለገሳቸውን ሆስፒታሉ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡ በተያያዘም ጤና ሚንስትር ዶ/ር ሊያ ታደሠ ወደ ሃገር ቤት በመምጣት ላይ እንዲሁም በያሉበት ሆነው የህክምና ግብዓቶችን በማሰባሰብ ለመላክ እየተዘጋጃችሁ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በጦርነቱ የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም እያደረጉት ለለው ርብርብ ምስጋና አቅርበዋል የህክምና መሳሪያዎች እና ግብአቶች ድጋፍ የርክክብ ሂደቱን የተሳለጠ ለማድረግ ሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ የመረከቢያ ቦታ ማዘጋጀቱን ዶ/ር ሊያ ታደሠ ተናግረዋል

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-21