የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ለህክምን ወደ አሜሪካ መሄዳቸውን ተከትሎ ቅርስ አሽሽተዋል በሚል የቀረበባቸው ሀሰተኛ ክስ በተመለከተ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ አብርሃም መግለጫ ሰጥተዋል።
በሀገር ውስጥና በውጭ ላለችው ቤተ ክርስቲያን አባት የሆኑ አባትን በዚህ መንገድ መናገር ሉዋላዊ የሆነች ቢተክርስቲያን እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምእመናንን መድፈር ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ቤተ ክርስቲያንን በመከፋፈል ትርፍ ማግኘት አይቻልም በማለት ግልፅነት ለመፍጠር ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር በቀጣይ እንወያያለን ብለዋል።
በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-27
