ሀገሬ ቲቪ

የአሜሪካ አፈ ጉባኤ ወደ ታይዋን መጓዝ ለደህንነታቸው አስጊ ነው ተባለ

የአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን የሚበሩ ከሆነ ቻይና አውሮፕላናቸውን ልታጠቃ ትችላለች የሚል ፍርሃት እንዳላቸው የሀሀሬው ሹማምንት ተነገሩ።

ይህንን ስጋት ለመቅረፍ ፔንታጎን የጥንቃቄ ዕቅድ እያዘጋጀ መኾኑ ተሰምቷል። ፔሎሲ ወደ ታይዋን የሚጓዙ ከሆነ የአሜሪካ መከላከያ በኢንዶ ፓስፊክ ቀጠና እንቅስቃሴው ሊጨምር ይችላል ተብሏል።

ውጥረት ወደ ተሞላበት ቀጠና የሚያደርጉት ጉዞ አደጋ ላይ ሊጥለው እንደሚችል ነው የተነገረው። ተዋጊ ጀቶች፣ መርከቦች፣ ሌሎችም ወታደራዊ መገልገያዎች አፈጉባኤዋን ለመጠበቅ ሊሳተፉ እንደሚችሉም አሶሽየትድ ፕረስ አስነብቧል።

በአብርሃም በለጠ
2022-07-27