ሀገሬ ቲቪ

የፈረንሳይ የቅኝ ግዛት ጊዜ የነበሩ የምስል ክምችቶችን ይፋ ልታደርግ ነው

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን በካሜሮን የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ጊዜ የነበሩ ማስረጃዎችን ወይም ክምችቶችን ክፍት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቱ የታሪክ ተመራማሪዎች ያለፈውን እንዲያጠኑ ጠይቀዋል።

አሳዛኝ ክስተቶችንም ይፋ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። በካሜሮን የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ጊዜ ያሉ ክምችቶችን ሙሉ ለሙሉ ክፍት እንደሚደረጉም ጠቁመዋል።

ማክሮን ይህን ያሉት በካሜሮን ዋና ከተማ ያኡንዴ ነው። ፕሬዝዳንቱ የሁለቱም ሀገራት የታሪክ ተመራማሪዎች በጋራ ያለፈውን እንዲያጠኑ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

በአብርሃም በለጠ
2022-07-27