ሀገሬ ቲቪ

ኢትዮ ቴሌኮም ከሶሥት ሺህ በላይ የኔትዎርክ ጣቢያዎች ከአገልግሎት ውጪ ኾነውብኛል አለ

ኢትይዮቴሌኮም የ2014 በጀት ዓመትን የሥራ አፈጻፀም ዛሬ ሀምሌ12 2004 ዓ.ም ይፋ አድርጓል።

ተቋሙ በሚሰጣቸው አገልግሎት ከባለፈው በጀት አመት ጋር በማነጻጸር ሪፖርቱን አቅርቧል። በዘንድሮ በጀት ዓመት የደንበኞቹን ቁጥር 66.59 ሚሊዮን ማድረሱን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪ ፍሬሕይወት ታምሩ ገልጸዋል።

ይህም የእቅዱን 104% ማሳካት መቻሉን አስታውቋል። ይኹን እንጂ በሀገሪቱ የነበረው ጦርነት ትልቅ ችግር ኾነውብኝ ነበር ብሏል። በዚሕም ከ3ሺህ በላይ የሞባይል ኔትዎርክ ጣቢያዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል።

ይህ ከአገልግሎት ውጪ የነበረው የኔትዎርክ ጣቢያ ተቋሙ ካሉት ጣቢያዎች በአጠቃላይ 45% ይሸፍናል። ከነዚህም ውስጥ የተወሰኑት ተጠግነው ዳግም ወደ አገልግሎት ገብተዋል።

በዚህ ሳቢያ በርካታ ሽፋን ባለባቸው አካባቢዎች የድምጽ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል።

ሌላው ተቋሙ በሪፖርቱ ያነሳው ጉዳይ በውጪ ምንዛሬ አገኝ የነበረው ገቢ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ጎደል ብሎብኛል ብሏል። በዚህ ዓመት 146.6 ሚሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሬ አግኝቻለሁ ብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም እነዚህ ሁሉ ፈተናዎች ቢገጥሙኝም ባጠቃላይ በዘንድሮ ዐመት 61.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-07-28