ደስታ ምንድ ነው? በምን ይለካል?
ይህ ጥያቄ በሰው ልጆች ሁሉ ዘንድ በእኩል ትርጉም ሊያገኝለት ከማይችላቸው ጥያቄዎች መካከል ነው።
ሁሉም ሰው በዚህ ምድር ላይ ሲኖር ደስተኛ ለመሆን በቻለው መጠን ሁሉ ይሞክራል።
ዛሬ የዓለማችን ደስተኛ ሰው እዚህ አለ መባሉን ሰማን እና ልናስተዋውቃችሁ ወደድን።
ይህ ሰው ማሪዮ ሳልሴዶ ይባላል።
ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በውቅያኖስ ላይ አሳልፏል።
የ65 ዓመቱ ማሪዮ በትልቋ ቅንጡ የመዝናኛ መርከብ ሮያል ካሪቢያን ላይ እህል ውሃውን አድርጎ እየኖረ ነው።
ሮያል ካሪቢያን አሁን በዓለማችን ካሉ መርከቦች ትልቋ ቅንጡ የመዝናኛ መርከብ ነች።
ማሪዮ ሳልሴዶ ወይም በመርከብ ላይ መጠሪያው ሱፐር ማሪዮ አሁን በዓለማችን ላይ ያለ ደስተኛ ሰው ነው ተብሎለታል።
ሱፐር ማሪዮ ወደ ዚህ ምርከብ ላይ እግሩ ከመውጣቱ አስቀድሞ መልቲ-ናሽናል ኮርፖሬሽን ለተባለ ኩባኛ በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ተቀጥሮ ይሰራ ነበር።
እድሜው 47 ሲደርስ ከድርጅቱ የተሰናበተው ማሪዮ በባህር ላይ አዲስ ህይወትን ለመጀመር በማሰብ ወደዚህች መርከብ ተሳፈረ።
እንደቀልድ የወሰነው ውሳኔ አስርት ዓመታት ኑሮውን ባይር ላይ አድርጎ አስቀርቶታል።
ከ9 ሺሕ በላይ ለሊቶችን በውቅያኖስ ላይ አሳልፏል።
ታዲያ ይህ አይነት የህይወት ዘይቤ በምድር ላይ እንደመኖር ቀላል አይደለም።
ሰዎች ከጉሮሯቸው ቀንሰው ክረምቱን በዚህች መርከብ ላይ ለማሳለፍ ይመጣሉ።
ማሪዮ ግን በምድር ሳለ ከሰበሰበው ገንዘብ ላይ በዚህ መርከብ ላይ ለሚያሳልፈው አንድ ዓመት ከ60 እስከ 70 ሺሕ ዶላር ለመክፈል ይገደዳል።
በዓመት ውስጥ ከ15 ቀናት ያልዘለለ ግዜን ብቻ በመሬት ላይ የሚያሳልፈው ማሪዮ፤ በመርካብ ላይ በነበረው ቆይታ የተነሳ ቀጥ ብሎ የመራመድ ችግር እንደሚያጋጥመው ይናገራል።
ዓለምን የፈተነው የኮቪድ 19 ወረርሺኝ መከሰቱን ተከትሎ የመርከቧ እንቅስቃሴ ሲገታ 20 ዓመታትን በመርከቧ ላይ ያሳለፈው ማሪዮም መሬትን የመርገጥ ግዴታ ውስጥ ገባ።
በርግጥ ኮቪድ 19 በዓለም ላይ መከሰቱን ተከትሎ ላለፉት 20 ዓመታት ከውሃ ርቆ በምድር ላይ ለመኖር የተገደደው ማሪዮ አሁን በድጋሚ ወደ መርከብ ኑሮው ተመልሷል።
በዚህ ውድ መርከብ ላይ ገንዘብን ማጥፋትህ ለምንድነው ለሚሉት ሁሉ፤ በምድር ላይ ደስተኛ መሆንን ብቻ ነው ምፈልገው ይላል ማሪዮ።
በሳምሶን ገድሉ
2022-07-28
