ሀገሬ ቲቪ

የኢራቅ ምክር ቤት

ሙቅታዳ አል-ሳድር የተባሉ የሃይማኖት መሪ ደጋፊዎች የኢራቅን ምክር ቤት ጥሰው ገቡ።

ከመቶ በላይ የሚገመቱ ተቃዋሚዎች የሃይማኖት መሪው ባለ አንጣ የሆኑትና ከኢራን ጋር ቅርበት አላቸው የሚባሉ ግለሰብ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እጩ መሆናቸውን አውግዘዋል።

ደጋፊዎቹ ሲዘፍኑ፣ ሲደንሱና በምክርቤቱ ጠረጴዛ ላይ እስከመተኛት ሲደርሱ ታይተዋል።

አልሳድር ከዚህ ቀደም በተካሄደው ምርጫ ድምጽ ቢያገኙም በተነሳው ፖለቲካዊ ውጥረት ሳቢያ ሥልጣን አለመያዛቸውን ሲኤን ኤን አስታውሷል ።

በመቅደስ እንዳለ
2022-07-28