ከ3500 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች እና ሴቶች የስራ እድል ይፈጥራል የተባለው አውደ ርዕይ ዛሬ በ ኤግዚቢሽን መዓከል ተከፍቷል ።
መላ ኢቨንት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ እና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር "ራዕዮን ይጨብጡ" በሚል መሪ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ አውደ ርዕይውን አዘጋጅቷል ።
በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ከ50 በላይ ቀጣሪ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን ሰራተኛ እና አሰሪ ከማገናኘት ባሻገር በዘርፉ ላይ ትኩረት ያደረገ አውደ ጥናት እንደሚከወን አዘጋጆቹ ነግረውናል ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-07-28
