ሀገሬ ቲቪ

11 ቢሊየን ዶላር ግብር የከፈለው ቱጃሩ ሞስክ

አሜሪካዊው ቢሊየነር ኤለን ሞስክ በዚህ ዓመት ብቻ ከ11 ቢሊየን ዶላር በላይ ታክስ ከፍያለው አለ። ቢሊየነሩ የሀገሪቱ ሴናተር የሆኑት ኤልዛቤት ዋረን ያስተላለፉበትን ወቀሳ ተከትሎ ነው ይህንን ያለው። ሴናተሯ በቲውተር ገጻቸው ሞስክ ሰዎች ላይ በነጻ መነገዱት አቁሞ ግብሩን በአግባቡ ይክፈል ሲሉ ወርፈውታል። ታዲያ ባለ ረብጣ ቢሊየነሩ ሲመልስ በዓመቱ በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛው ቀረጥ ከፋይ ነኝ ብሏል። ቢሊየነሩ ለአሜሪካ መንግስት ከፍያለው ያለው ገንዘብ ወደ ብር ሲለወጥ 528 ቢሊየን ብር ይሆናል። ይህም ኢትዮጵያ ለ2014 በጀት ዓመት ከያዘችው 561 ቢሊዮን ብር በጀት በ33 ቢሊየን ብር ወይም በ2 ቢሊየን ዶላር ብቻ ያነሰ ነው። የቢሊየነሩ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ኩባንያ ቴስላ አሁን ባለው ገበያ አንድ ትሪሊየን ዶላር ሲገመት በዓመቱ ቢሊየነሩ ወደ 14 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብን ከመኪና ኩባንያው የአክሲዮን ሽያጭ ሰብስቧል።

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-21