የፋርማሲ ሙያ የመድኃኒት ሥርጭትና ቆጠራ ላይ ብቻ ከሚያነጣጥር፣ የበሽተኛና የመድኃኒት የምክር አገልግሎት ላይ ያተኮረ መሆን እንዳለበት የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ሆስፒታሎች ደግሞ በየሕሙማን መኝታ ክፍሎች በፋርማሲስቶች ሊከናወኑ የሚችሉ ብዙ ሥራዎች እንዳሉም ይገለጻል።
ስለዚህ ተጨማሪ የስራ ሃላፊነት መስጠት ያስፈልጋል። የሌሎች ሀገሮች ልምድንም ስንመለከት ይህንኑ ያሳየናል።
አቶ ተስፋዬ ሰይፉ የኢትዮጵያ ፋርማሲ ማኅበር ፕሬዚዳንት ናቸው ። የፋርማሲ ባለሙያዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ከመሆናቸው አንጻር በሚገባ ሚናቸውን እየወጡ ነው ለማለት አያስደፍርም ብለውናል።
ባለሙያዎቹ ተጨማሪ ስራዎችን እንዲሰሩ የተዘጋጀ የህግ ማዕቀፍ አለመኖር ዘርፉን እየጎዳው እንደሆነ አቶ ተስፋዬ አስረድታውናል።
የጤና ሚኒስቴር አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ሙኒር ካሳ በበኩላቸው የህግ ማእቀፉን ለማዘጋጀት መሟላት የሚገባቸው ነገሮች አሉ ብለውናል
ከ20 ሺህ በላይ የፋርማሲ ባለሙያዎች በሀገራችን እንዳሉ ይገመታል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-07-29
