ሀገሬ ቲቪ

ባይደን እና ዢ ጂንፒንግ ማስጠንቀቂያ ተለዋወጡ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና የቻይና አቻቸው ዢ ጂንፒንግ በታይዋን ጉዳይ የሁለት ሰዓት የስልክ ንግግር አድርገዋል። በውይይታቸው ስለ ታይዋን ጉዳይ ማስጠንቀቂያወችን ተለዋውጠዋል።

ባይደን አሜሪካ የታይዋንን ሁኔታ የሚቀይር የአንድ ጎን እንቅስቃሴን አጥብቃ እንደምትቃወም ተናግረዋል። ደሴቷን የሚመለከተው የአሜሪካ ፖሊሲም እንዳልተቀየረ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ዢ በበኩላቸው ባይደን የአንድ ቻይና ፖሊሲን እንዲያከብሩ በእሳት የሚጫወት ይቃጠላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በአብርሃም በለጠ
2022-07-29