ሀገሬ ቲቪ

የአፕል እና አማዞን ሽያጭ ጨምሯል ተባለ

የቴክኖሎጂ ተቋማቱ የአፕል እና የአማዞን ሽያጭ መጨመሩ ተገለጸ። ምንም እንኳን ሁለቱ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት የዋጋ ጭማሬ ያደረጉ ቢሆንም ሽያጫቸው መጨመሩ ነው የተጠቆመው።

አማዞን እና አፕል ከተገመተው ሽያጭ በላይ ማስመዝገባቸውን ነው ገልጸዋል። ትልልቅ የኢኮኖሚ ተቋማት አለም አቀፍ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን ማለፍ እንደሚችሉ ማሳያም ነው ተብሏል።

ሁለቱ ተቋማት በፍጥነት የዋጋ መጨመር እየታየ ቢሆንም የማምረቻ ወጭዎችን ለመቆጣጠር እየሰሩ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

በአብርሃም በለጠ
2022-07-29