ሀገሬ ቲቪ

የላይኛው አዋሽ ተፋሰስን በዓለም ቅርስነት የማስመዝገብ እንቅስቃሴ ተጀመረ

የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን የላይኛው አዋሽ ተፋሰስ አካባቢን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ለተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ጥያቄ አቅርቤያለሁ አለ።

የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው ቅርሱ ዝርዝር እጩዎች ውስጥ መካተቱን ለጣቢያችን ተናግረዋል።

አሁን ላይም አካባቢውን የሚመለከቱ መረጃዎችን የማደራጀት ስራ እንደተጀመረ ጠቅሰው በ2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ እንደታሰበ አውርተውናል።

የላይኛው አዋሽ ተፋሰስ የጥንት የሰው ልጅ ዝሪያ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ጥንታዊ የድንጋይ መሳሪያዎችን የያዘ አካባቢ ነው።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-01