ሀገሬ ቲቪ

የናይጄሪያ ፖሊስ አስጠነቀቀ

የናይጄሪያ ፖሊስ ያለቅድመ ፍቃድ የናይጄሪያ ፖሊስ መኮንኖችን በመጥፎ ሁኔታ የሚያሳዩ ፊልሞች እንዳይሰሩ አስጠነቀቀ።

የሀገሪቱ ፖሊስ ዋና ኢንስፔክተር ኡስማን ባባ እንዳሉት የፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ ተዋናዮች በፊልም ትዕይንት ውስጥ በህግ በተቀመጠው መሰረት ጥፋተኞችን በህግ ሲጠየቁ ማሳየት አለበት ብለዋል።

ትዕዛዙ በፖሊሶች ዙሪያ ያሉትን የተሳሳቱ አመለካከቶች ለማረም ነው ተብሎለታል። የናይጄሪያ የፊልም ኢንደስትሪ ተብሎ የሚጠራው ኖሊውድ ለመላው አፍሪካ ፊልም አፍቃሪያን ግብዓት የሚሆኑ ፊልሞችን በየጊዜው ያቀርባል ።

በፊልሞቹም የፖሊስ መኮንኖች ገጸ ባህሪ በብዛት ያሳያል ሲል ኤኤፍፒ ጽፏል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-01