ሀገሬ ቲቪ

ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በሀገር ውስጥ የመሸፈን ውጥን

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋና በምዕራብ አርሲ ዞኖች በ አስር ወረዳዎች 24ሺ ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል የምስራቅ ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ መስፍን ተሾመ እንደገለጹት በዞኑ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በወረዳዎቹ 35ሺ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እስካሁን 24ሺ ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል በጦርነቱ ያጣነውን ምርት በሚያካክስ መልኩ በስፋት በመስራት ምርታማነትን የማሳደግ ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል ሃላፊው፡ ወደ ግንባር ለዘመቱ አርሶ አደሮች እየተሠራ ያለው ሰብል የመሰብስብ ስራን በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው የተናገሩት በዞኑ በአዳማ ወረዳ ወንጂ ኩሪፍቱ ቀበሌ 500 ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም ስንዴ እየለማ መሆኑንም ጠቁመዋል በተመሳሳይ በክልሉ በምዕራብ አርሲ ዞንም በተመሳሳይ በበርካታ ቀበሌዎች በበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት ተግባራዊ በማድረግ በከፍተኛ ወጪ ከውጪ የሚገባውን ስንዴ ለማስቀረት በከፍተኛ ተነሳሽነትና እየተሰራ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በዞኑ በ8 ወረዳዎች ባሉት ቀበሌዎች ከ12ሺ ሄክታር መሬት በላይ ለማልማት የታቀደ ሲሆን በዚህም አፈፃፀም እሰካሁን ከ9ሺ ሄክታር በላይ በዘር በመሸፈን አርሶ አደሩ የመንከባከብ ስራ እሰራ ይገኛል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-21