መቼም ሰዎች ነን እና ህመም አያጋጥመን ማለት አይቻልም። ለህመማችን መድሃኒቱን መፈለግ የህመሙን ምንጭ ከማወቅ ይነሳል። አመጋገብ ደግሞ በሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠሩ ነገሮችን መልካምም ህመምም እንዲሆኑ ያደርጋል።
በሆድ ቁርጠት የተሰቃየ ሰው ለህመሙ መነሻ አደረገ የተባለው ነገር በርካቶችን ወይ ጉድ አሰኝቷል። ሰውየው መከራ ለሆነበት የሆድ ህመም ከዓመታት አስቀድሞ የበላው ሳንዱች ነው ባይ ነው።
ነገሩ የሆነው ከ5 ዓመታት በሰሞነ ገና በሀገረ እንግሊዝ ነው። ታይሮን ፕራዴስ የተባለው ይህ ሰው ከቤተሰቦቹ ጋር እንግሊዝን እየጎበኘ በነበረበት ሰዓት ነው።
ለመዝናናት በሚል በእንግሊዝ ጎዳናዎች ተወዳጅ ወደ ሆነው እና ወደ ማይጠፋው የሳንዱች መሸጫ ድንኳኖች ጎራ ይላሉ። ያማራቸውን የሳንዱች አይነት አማርጠውም ከቤተሰቡ ዳር ይመገባሉ።
ታይሮን ሳንዱቹን ከበላ ከሰዓታት በኋላ ሆድ ቁርጠት፣ ማስመለስ፣ ማስቀመጥ እና ትኩሳት ያጣድፈዋል። የ46 ዓመቱ ሰው ከዚያን እለት በኋላ የስቃይ ቀናትን እያሳለፈ ስመመሆኑ ይናገራል።
ጎልማሳው ታይሮን አሁን ድረስ ከባድ በሆነ የሆድ መነፋት እና አይደለም ለሰው ለራሱ እራሱ የሚያስደነግጠው የሆድ ድምፅ እየተሰቃየ ነው ነው የተባለው። በውድቅት ሌሊት ታይሮን በገዛ የሆድ ድምፁ ባኖ ንመነሳትን ተለማምዷል።
ታዲያ ታይሮን የዛን ሳንዱች መሸጫ ድንኳን ባለቤትን ከሶታል። ለደረሰብኝ ጉዳትም 243 ሺህ ዶላርሊከፈለኝ ይገባልም ሲል።
የታይሮን ጠበቃ እንዳሉት ከሆነ ደግሞ ድካም እና እንቅልፍ ለመተኛት እስከመቸገር የደረሰ የሆድ ድምፅ ለደንበኛቸው ዓመታትን በስቃይ እንዲያሳልፍ ምክኛት ሆነዋል ብሏል።
ታይሮን ጤናዬን ላጣሁበት ካሳ ይገባኛል ብሎ ፍርድ ቤት ቢቆምም ያለፉትን 5 ዓመታት እረፍት የነሳው ህመሙ ዛሬም ከሰዎች መሀል አብሮ እንዳይቆም ሰበብ ሆኖት ዛሬም አለ።
በሳምሶን ገድሉ
2022-08-01
